AMN- ኅዳር 7/2019 ዓ.ም
በመርካቶ የበጎነት መንደር (በቅጠል ተራ) የተገነቡት ዘጠኝ የመኖሪያ ቤት ሕንፃዎች ከተራ የግንባታ ሥራ በላይ የዜጎችን የኑሮ ሁኔታ የሚቀይሩ፣ የቤተሰቦችን ተስፋ የሚያድሱና ማህበራዊ ፍትህን በተግባር የሚያረጋግጡ ትልልቅ ማሳያዎች ናቸው።
የቤት እጦት ችግርን መቅረፍ ማለት የአንድን ቤተሰብ ነገን መገንባት፣ የልጆችን የተሻለ ዕድል ማረጋገጥ፣ የኑሮ ደህንነትን ማጠናከር እንዲሁም የአካባቢውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ገጽታ ማነቃቃት ነው።
በመሆኑም ይህ ልማት ከአንድ ቤት ባለቤት ከማድረግ በላይ የዘለቀ ትልቅ ማህበራዊ እሴት አለው።
ዜጎች የተሻለ ኑሮ እንዲኖሩ፣ ቤተሰቦች በኢኮኖሚያዊ ጫና ሳይገደቡ የወደፊት ዕቅዳቸውን እንዲያሳኩ፣ ማህበረሰቡም በመተሳሰብና በአንድነት እንዲጠናከር የሚያግዝ ተጨባጭ ለውጥ እውን ሆኗል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማ ልማት ትግበራዎችን ከዜጎች ትክክለኛ ፍላጎት ጋር በማቀናጀት ቃልን በተግባር እያረጋገጠ ይገኛል።
የከተማ አስተዳደሩ የነዋሪዎችን ኑሮና አኗኗር ለማሻሻል በቀን 24 ሰዓት እና በሳምንት 7 ቀናት በልዩ ትኩረት እየሰራ ይገኛል።
የከንቲባ ጽ/ቤት