የኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ዛሬ ሞሮኮን ይገጥማል

You are currently viewing የኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ዛሬ ሞሮኮን ይገጥማል

AMN-ኅዳር 3/2019 ዓ.ም

‎የኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ለአፍሪካ ከ23 ዓመት በታች ውድድር ለማለፍ የሁለተኛ ዙር የመጀመሪያ ጨዋታውን ዛሬ ከሞሮኮ አቻው ጋር ያደርጋል።

በአሰልጣኝ ዳንኤል ፀሃዬ የሚመራው ብሔራዊ ቡድኑ ለበርካታ ቀናት በአዲስ አበባ እና ድሬዳዋ ከተማ ዝግጅቱን ሲያደርግ ቆይቷል።

ብሔራዊ ቡድኑ በትናንትና ዕለት የመጨረሻ ልምምዱን በድሬዳዋ ስታዲየም ሲያደርግ የእግር ኳስ ፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ ተገኝተው ልምምዱን ተከታትለዋል። ተጫዋቾች እና የአሰልጣኝ ቡድን አባላትንም አበረታተዋል።

በኢትዮጵያ እና ሞሮኮ መካከል የሚደረገው ከ23 ዓመት በታች አፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ የሁለተኛ ዙር የመጀመርያ ጨዋታ ዛሬ ከቀኑ 10፡00 ጀምሮ ይካሄዳል።

ጨዋታውን ማዳጋስካራዊው ‎ዳኛ አንድሪሶ ዘፋማሃቶሃ በዋና ዳኝነት ይመሩታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review