AMN – ጥቅምት 21/2017 ዓ.ም
ባለፉት ሶስት ወራት 180 ቢሊዮን ብር ገቢ መሰብሰቡን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡
6ኛው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ብ 4ኛ ዓመት 3ኛ መደበኛ ስብሰባ እየተካሄደ ነው፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከምክር ቤት አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽ እየሰጡ ነው፡፡
ገቢን በተመለከተ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሰጡት ማብራሪያ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ተከትሎ የመንግስት ገቢ በእጅጉን ጨምሯል ብለዋል፡፡
ባላፉት ሶስት ወራት 180 ቢሊዮን ብር ገቢ መሰብሰብ መቻሉን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህም ካለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጻር የተሻለ እድገት የተመዘገበበት መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
በ2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያዎቹ ሶስት ወራት የተሰበሰበው ገቢ 109 ቢሊዮን ብር ብቻ እንደነበርም አስታውሰዋል፡፡
ኢትዮጵያ ከአጠቃላይ የሀገር ውስጥ ጥቅል ምርት አንጻር ዝቅተኛ ገቢ የምትሰበስብ ሀገር መሆኗን በማንሳት በቀጣይ መሻሻል እንዳለበት አስገንዝበዋል፡፡