
AMN – ጥቅምት 28/2017 ዓ.ም
“ረሃብን መዋጋት የጋራ ምላሽን ይሻል” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡
ለዚህም ለምግብ ዋስትና የሚሆን የአለምአቀፍ ድጋፍ አቅርቦት፣ ድንበር ዘለል የሆነ የእውቀት ማካፈል ልምምድ፣ ለፍትሃዊ ተደራሽነት የሚረዳ የፖሊሲ መናበብ ብሎም ለሴቶች ትኩረት የሚሰጥ የአነስተኛ አርሶና አርብቶአደሮች ድጋፍ ሥራ አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ፣ የ ’World Without Hunger’ ጉባኤ እጅግ ጠቃሚ የሆኑ ውይይቶች የተሳኩ ይሆኑ ዘንድ አስተዋፅዖ ያበረከቱ ተሳታፊዎችን አመስግነዋል፡፡
አርባ ቢሊዮን ዛፎች በተተከሉበት ምርታማነትን በሚያሳድጉ የለውጥ ሥራዎች፣ ድርቅን በሚቋቋሙ አዝርዕት ልማት፣ በ #አረንጓዴዓሻራ መርሃ ግብር ሥራዎች አማካኝነት በዘላቂ የግብርና ሥራ የታየው የኢትዮጵያ ርምጃ በጉባኤው መቅርቡን ገልጸዋል።

በ’ኢትዮጵያ ታምርት’፣ በአግሮ ኢንደስትሪ ፓርኮች ጥምር የሥራ ፈጠራ ሥራ፣ በገቢ እድገት እና ጽናት የታዩት ኢንቨስትመንቶች በአለም የግብርና ዘርፍ የኢትዮጵያን ሚና አጠናክረውታልም ብለዋል።