AMN- ነሐሴ 1/2018 ዓ.ም

የኦሮሞ ሕዝብ የዘመናት የማንነትና የኢኮኖሚ ጥያቄዎች በአሁኑ ወቅት ምላሽ እያገኙ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትዎርክ (OBN) ጋር ቆይታ አድርገዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኦሮሞ ህዝብ ለምን ታገለ? በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ ማብራሪያና ምላሽ ሲሰጡ፤ የኦሮሞ ሕዝብ ትግል የብዙ ዘመናት መሆኑን ገልጸዋል።

ኦሮሞ በሦስት ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ መታገሉን ያስረዱት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ፤ ጥያቄዎቹም የኢኮኖሚ፣ የማንነት እና የዲሞክራሲ ጥያቄ መሆናቸውን ተናግረዋል።
ትግሉ ውጤት እንዲያገኝ ኦሮሞ ለረጅም ዓመታት መታገሉን በመግለፅ፤ ዛሬም ቢሆን ኦሮሞ የታገለለት ነገር ሙሉ በሙሉ ተመልሷል ባንልም አሁን ግን ከመሠረቱ እየተመለሰ መሆኑን አንስተዋል።
ነገር ግን የኦሮሞ ትግል ሙሉ በሙሉ ፍሬ እንዳያፈራ ከባድ እንቅፋት ከሆኑት ነገሮች መካከል በመንደርና በበጎጥ መከፋፈል እንደሆነ ጠቅሰው፤ ይህም ኦሮሞ የታገለለት ዓላማ በፍጥነት ከመሳካት ይልቅ ለብዙ ዓመታት በትግል ውስጥ እንዲቆይ ያደረገው መሆኑን በቆይታቸው አንስተዋል።
ኢዶሳ አብዲ