ለመጪዎቹ በዓላት የጤፍ አቅርቦት በተመጣጣኝ ዋጋ እና በስፋት እየቀረበ ነው፡- የአዲስ አበባ ህብረት ስራ ኮሚሽን

You are currently viewing ለመጪዎቹ በዓላት የጤፍ አቅርቦት በተመጣጣኝ ዋጋ እና በስፋት እየቀረበ ነው፡- የአዲስ አበባ ህብረት ስራ ኮሚሽን

AMN – ታኅሣሥ 17/2017 ዓ.ም

ለመጪዎቹ በዓላት የጤፍ አቅርቦት በተመጣጣኝ ዋጋና በስፋት እየቀረበ መሆኑን የአዲስ አበባ ህብረት ስራ ኮሚሽን አስታወቀ።

በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ ዩኒየኖች በኦሮሚያ ክልል የሚገኘውን የሊበኒ ገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒየን የምርት አቅርቦትን ወሊሶ በሚገኘው መጋዘንእና በአርሶ አደሮች ማሳ ላይ ያለውን የጤፍ ምርት ተመልከተዋል።

ገናን ጨምሮ ለመጪዎቹ በዓላት የከተማዋ ነዋሪ የእለት ተዕለት የጤፍ ፍላጎትን ማሟላት የሚችል የምርት አቅርቦት እንዲኖር ዩኒየኖች ከአምራች አቻ ዩኒየኖች ጋር ትስስር በመፍጠር እየሰሩ ይገኛል።

የከተማዋ ህብረት ስራ ኮሚሽንም ዩኒየኖች ከክልል አምራች ዩኒየኖች ጋር ተቀራርበው የከተማዋን ፍላጎት እንዲያግዙ እና ገበያን እንዲያረጋግጉ እየደገፈ ነው።

ከተለያዩ ክልሎች ጋር በሚፈጠር ትስስርም ምርት በብዛት ወደ ከተማዋ እየገባ መሆኑ ተመልክቷል።

ኮሚሽኑ የምርት አቅርቦት ምን እንደሚመስልም ከዩኒየኖች ጋር በመሆን በክልሎች ያለውን የምርት አቅርቦት ተመልክቷል።

በወሊሶ ከተማ የሚገኘው የሊበኒ ገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒየንም ከአባል አርሶ አደሮቹ የጤፍ ምርትን በስፋት እየሰበሰበ እንደሚገኝ ገልጿል።

ዘንድሮ የጤፍ ምርት በስፋት በመኖሩ በተመጣጣኝ ዋጋ የሚሰበሰበውን ጤፍ 95 በመቶ ለአዲስ አበባ ከተማ እያቀረበ መሆኑን ነው የዩኒየኑ ስራ አስኪያጅ አቶ ደሳለኝ አያንሳ የተናገሩት።

የአዲስ አበባ ህብረት ስራ ኮሚሽን ም/ኮሚሽነር ሀብተየስ ዲሮ እንዳሉት የክልል አምራች ዩኒየኖች በቀጥታ ለከተማዋ ዩኒየኖች ምርቶቻቸውን እንዲያቀርቡ ትስስር በመፍጠር በቅንጅት እየተሰራ ነው።

ጥራት ያለው የጤፍ ምርት በተመጣጣኝ ዋጋ በስፋት እንዲቀርብም ትስስሩ ሚናው የላቀ ነው ያሉት ም/ኮሚሽነሩ ዩኒየኖችን በመደገፍ በቂ ምርት እንዲይዙ እየተደረገ ነው ብለዋል።

ወቅቱ የሰብል ምርት በብዛት የሚገኝበት በመሆኑም ሁሉም ዩኒየኖች በየመጋዘኖቻቸው የምርት ክምችት እንዲኖራቸው እየተደረገ መሆንኑ ጠቁመዋል ም/ኮሚሽነሩ።

የሊበኒ የገበሬዎች ህብረት ስራ ማህበር ጤፍን ከ10 ሺህ እስከ 10 ሺህ አምስት መቶ ብር እያቀረበ ነው።

በፍቃዱ መለሰ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review