AMN- ነሐሴ 10/2018 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለ2027 የአፍሪካ ዋንጫ የመጀመርያ የምድብ ማጣርያ ለሚያደርጋቸው ጨዋታዎች ልምምድ ጀምሯል።

ተጫዋቾቹ ትናንት የስብ መጠን እና ተያያዥ ምርመራዎች በዶ/ር ኤልያስ አቢሻክራ አማካኝነት የተደረገለቻው ሲሆን በዛሬው ዕለት ደግሞ በአዲስ አበባ ስታዲየም የአካል ብቃት ምዘና አከናውነዋል።

ጥሪ ከተደረገላቸው ተጫዋቾች መካከል 31 ተጫዋቾች በስብስብ ውስጥ የሚገኙ ሲሆን የሲዳማ ቡና እንዲሁም በውጪ ሀገር ክለቦች የሚገኙ ተጫዋቾች በቀጣይ ጊዜያት ብሔራዊ ቡድኑን እንደሚቀላቀሉ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ገልጿል።