አርሰናል ማንችስተር ሲቲን 3ለ0 አሸነፈ

AMN- ነሐሴ 10/2018 ዓ.ም

አርሰናል በኮሚኒቲ ሺልድ ጨዋታ ማንችስተር ሲቲን 3ለ0 በማሸነፍ የዋንጫ ባለቤት ሆኗል። የሰሜን ለንደኑ ክለብ ብልጫ በወሰደበት ጨዋታ ሪካርዶ ካላፊዮሪ ፣ ካይ ሃቨርትዝ እና ማርቲን ኦዴጋርድ ሦስቱን ግቦች አስቆጥረዋል።

የፕሪምየር ሊጉ አሸናፊ አርሰናል ድሉን ተከትሎ የኮሚኒቲ ሺልድን ለ18ኛ ጊዜ ማሳካት ችሏል። አርሰናል በኮሚኒቲ ሺልድ 21 ጊዜ የዋንጫ ባለቤት በሆነው ማንችስተር ዩናይትድ ብቻ ነው የሚበለጠው።

በካርዲፍ ሚሊኒየም ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ሲቲ የተወሰኑ የግብ ዕድሎችን ቢፈጥርም ያሳየው እንቅስቃሴ ደካማ የሚባል ነው። ስኬታማውን አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ በኢንዞ ማሬስካ የተኩት ሲቲዎች ብዙ የቤት ስራ ይጠብቃቸዋል።

አርሰናል በቀጣይ የፊታችን አርብ ኮቨንትሪ ሲቲን በሜዳው ኤምሬትስ በመግጠም ፕሪምየር ሊጉን ይጀምራል። ማንችስተር ሲቲ በአንፃሩ ቦርንማውዝን ያስተናግዳል።

በሰዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review