አዳነች አቤቤ
AMN – ጥር 29/2018 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለትዉልድ ግንባታ ቅድሚያ ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከምክር ቤት አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
ከተማሪዎች ምገባ ጋር በተያያዘ በትምህርት ቤቶች የሚከናወነው የተማሪዎች ምገባ በመንግሥት ፖሊሲ እና አቅጣጫ የተያዘ በመሆኑ ዘላቂነቱ አያሳስብም ብለዋል፡፡
መንግስት ከሕዝብ የሚሰበስበው በጀት ትውልድን ለመገንባት ከሚያውለው የሚበልጥ ጉዳይ የለም ያሉት ከንቲባዋ ተማሪዎች በምግብ ጉዳይ ከትምህርት ገበታቸው ሊርቁ እንደማይገባም ገልጸዋል፡፡
ለተማሪዎች ምገባም ያለምን እርዳታ በዓመት ከ4 ቢሊየን ብር በላይ በጀት ተመድቦ እየተሰራ መሆኑን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገልጸዋል፡፡
ትምህርት ቤቶች ባላቸው አቅም ገቢያቸውን እንዲያሳድጉ እና ከገቢያቸው መጠቀም እንዲችሉ አስራር መቀመጡንም አብራርተዋል፡፡
በተለይ በከተማ ግብርና ሞዴል የሆኑ ስራዎች በትምህርት ቤቶች እየተሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡
በታደሰ ሽፈራው