የትንሳኤ በዓልን ስናከብር እርስ በራስ በመረዳዳት እና አቅመ ደካሞችን በመደገፍ ሊሆን እንደሚገባ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ቡዜና አልከድር ገለጹ።

You are currently viewing የትንሳኤ በዓልን ስናከብር እርስ በራስ በመረዳዳት እና አቅመ ደካሞችን በመደገፍ ሊሆን እንደሚገባ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ቡዜና አልከድር ገለጹ።

የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ በአብርሆት ቤተ መጻህፍት ለአቅመ ደካማ አረጋውያን የጾም ማስፈሰክ መርሃ ግብር ተካሂዷል።

በመርሃ ግብሩ ላይ በመገኘት ማዕድ ያጋሩት የአዲስ አበባ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ እና የአብርሆት ቤተ መጻህፍት ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሮ ቡዜና አልከድር፤ የጾሙን ወቅት በጸሎት ያሳለፉ አረጋውያን በትንሳኤ ዕለት በትውፊቱ መሠረት በሌሊት የማስፈሰክ መርሃ ግብር በአብርሆት ቤተ መጻህፍት ባለፉት ዓመታት ሲካሄድ መቆየቱን አስታውሰዋል።

አፈ ጉባኤዋ አክለውም እንዲህ ዓይነቱ በዓልን በጋራ የማክበር መርሃ ግብር ሊስፋፋና ሊጠናከር እንደሚገባ ተናግረዋል።

ኅብረተሰቡ በዓልን ሲያከብር በአካባቢው ያሉ አቅመ ደካሞችንና ለተለያዩ ማህበራዊ ችግሮች የተጋለጡ ወገኖችን በማሰብ፣ እርስ በርስ በመረዳዳትና በመደጋገፍ ሊሆን እንደሚገባም አሳስበዋል።

በሰብስቤ ባዩ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review