AMN ግንቦት 18/2018
በአማራ ክልል በሚገኙ ታላላቅ ከተሞች የብልጽግና ፓርቲ ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ የማጠቃለያ መርሃ ግብር በመካሄድ ላይ ይገኛል።
በመርሃ ግብሩ መካሄድ የጀመረውም በባህርዳር፣ በጎንደር፣ በደሴ፣ በኮምበልቻ፣ በደብረ ብርሃን፣በመተማና በሌሎች ዋና ዋና እንዲሁም መካከለኛ ከተሞች ነው።
በሰልፉ ላይ የተለያዩ መፈክሮች እየተሰሙ ሲሆን ከደቂቃዎች በኋላ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በመገኘት መልዕክት ያስተላልፋሉ ተብሎ እየተጠበቀ ነው።

ከፍተኛ የፌደራልና የክልል አመራሮችም በሚወዳደሩባቸው ከተሞች በመገኘት ለመራጩ ህዝብ መልእክት እንደሚያስተላልፉም ታውቋል።