AMN- ሰኔ 14/2018 ዓ.ም

የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ውጤት ማሳወቂያ መርሐ ግብር በአዲስ አበባ ስካይ ላይት ሆቴል እየተካሄደ ይገኛል።
7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የውጤት ማሳወቂያ ሂደት ላይ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ተስፋዬ ንዋይ፣ ምርጫው ለፓለቲካ ፓርቲዎች እኩል እድል የሰጠ እንደነበር ገልፀዋል።

የፖለቲካ ፓርቲዎች ፖሊሲያቸውንና ያላቸውን ሀሳብ ለህዝብ እንዲያቀርቡ በ7 ሚዲያዎች የምርጫ ክርክር መድረክ ተዘጋጅቶላቸው በእኩልነት ሀሳባቸውን አቅርበዋል ብለዋል።
ከዚህ ባሻገር በምርጫው የፓለቲካ ፓርቲዎች የምርጫውን ፍትሀዊነት ለማስጠበቅ በታዛቢነት ጭምር እንዲሳተፉ ተደርገዋል ሲሉ አቶ ተስፋዬ ገልፀዋል።

ከዚህ ባሻገር ተወዳዳሪዎች በምርጫ ሂደቱ ያላቸውን ቅሬታ በጊዜውና በፍጥነት በመቀበል ለቅሬታዎች መፍትሄ ተሰጥቷል ሲሉ ጠቅሰዋል።
ከምርጫው ሂደት ጋር ተያይዞ የቀረቡ 129 ቅሬታዎችም በአግባቡ መፈታተታቸውን ገልጸዋልዋል።
በንጉሱ በቃሉ