AMN ሰኔ 18/2018
ፓኪስታን በ7ኛው የኢትዮጵያ ጠቅላላ ምርጫ ላሸነፈውና በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለሚመራው ብልፅግና ፓርቲ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፋለች።
የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሼህባዝ ሸሪፍ በመልዕክታቸው፣ ፓኪስታን እና ኢትዮጵያ በየጊዜው እያደገ የመጣ ጠንካራ ግንኙነት እንዳላቸው ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ሼህባዝ ሸሪፍ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እና ለኢትዮጵያ ሕዝብ ቀጣይነት ያለው ሰላም፣ ዕድገትና ብልፅግና ተመኝተዋል።
በተጨማሪም በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ወዳጅነት እና ትስስር ይበልጥ ለማጠናከር በጋራ ለመሥራት ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።