በፀጥታ፣ ሰላም እና የህግ የበላይነትን በማስከበር ስራዎች ምን ዉጤቶች ተገኙ?

AMN ሐምሌ 7/2018

👉 ባለፉት አምስት ዓመታት ከ200 ሺህ በላይ የሠላም ሠራዊት አባላት ተደራጅተዋል፤

👉 ከ10 ሺህ በላይ የህዝብ ቅጥር ጥበቃ በማደራጀት፣ በማሰልጠንና በማሰማራት ህዝባዊ ሚናቸውን እንዲወጡ ተደርጓል፤

👉 የጸጥታ መዋቅሩ፣ የሰላም ሰራዊት አደረጃጀቱ እና ነዋሪው በቅንጅት በመስራት ላይ ይገኛሉ፤

👉 በየጊዜው የሚነሱ የጸረ ሰላም ኃይሎችን ትንኮሳ ማምከን ተችሏል፤

👉 አስተማማኝ እና ዘላቂነት ያለው ስራ በመሰራቱ መዲናዋ “ የሰላም ከተማ ” በመባል በምሳሌነት ተጠቃሽ ሆናለች፤

👉 ደንብ መተላለፎችን የመከላከልና የመቆጣጠር ስራዎች ተጠናክረዉ ቀጥለዋል፤

👉 በከተማዋ የሚታዩ ህገ-ወጥ ድርጊቶችን በከፍተኛ ሁኔታ መቀነስ ተችሏል፤

👉 ህገ-ወጥ የመሬት ወረራ፤ ህገ-ወጥ ማስታወቂያ ፣ ህገ-ወጥ የጎዳና ንግድ፣ ህገ-ወጥ እንስሳት ዝውውርና እርድን መቀነስ ተችሏል

👉 ህገ-ወጥ የመንገድ አጠቃቀም፤ ህገ-ወጥ የግንባታ የቁጥጥር ስራዎችን ጨምሮ የተለያዩ የደንብ መተላለፎችን በዘላቂነት መቀነስ ተችሏል

👉 የነዋሪውን ንብረትና መብት ማስከበር ላይ መሰረታዊ ለውጥ ተመዝግቧል

👉 ሰላምን የማወክና ግጭት የማስነሳት እኩይ እቅዶችና ፍላጐቶች ቢያጋጥሙም መዲናዋ ፍፁም ሰላማዊ ሆናለች፤

👉 የከተማዋን ሰላም አስተማማኝ ማድረግ ተችሏል

👉 የህግ የበላይነትን ማረጋገጥ ተችሏል

👉 የከባድ ወንጀል ምጣኔ ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር ከ 47% በላይ እንዲቀንስ ማድረግ ተችሏል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review