የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ጉባዔ ሂደትን እና ዓላማ የአፍሪካ ሕብረት ያደንቃል – አምባሳደር ባንኮሌ

You are currently viewing የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ጉባዔ ሂደትን እና ዓላማ የአፍሪካ ሕብረት ያደንቃል – አምባሳደር ባንኮሌ

AMN-ሐምሌ 8/2018 ዓ.ም

ሙሉ በሙሉ በኢትዮያውያን አስተባባሪነትና ተሳታፊነት እየተከናወነ ያለውን ሀገራዊ የምክክር ጉባዔ የአፍሪካ ሕብረት ያደንቃል ሲሉ በሕብረቱ የፖለቲካ ጉዳዮች፣ የሰላምና ደኅንነት ኮሚሽነር የሆኑት አምባሳደር ባንኮሌ አዶዬ ገለጹ፡፡

በኢትዮጵያ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የሀገራዊ ምክክር ጉባዔ “በምክክር የምትጸና ሀገር” በሚል መሪ ሐሳብ በአዲስ ኮንቬንሽን ሴንተር መካሄድ ጀምሯል፡፡

በዚሁ ወቅትም የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽንን ወክለው በአፍሪካ ሕብረት የፖለቲካ ጉዳዮች፣ የሰላምና ደኅንነት ኮሚሽነር የሆኑት አምባሳደር ባንኮሌ አዶዬ ባደረጉት ንግግር ፣ ጉባዔው ልዩ እና ታሪካዊ መሆኑን አንስተዋል፡፡

እንደ ሕብረቱ ተወካይም ልዩ በሆነው እና ለአኅጉሪቱም ኩራት ሊሆን በሚችለው ጉባዔ ላይ ተገኝተው ንግግር በማድረጋቸው ኩራት እንደሚሰማቸው ገልጸዋል፡፡

ይህ ሀገራዊ ምክክር ታሪካዊ ድል ነው ያሉት አምባሳደር ባንኮሌ ፤ ለዘላቂ ሰላም እና ልማትም ከፍተኛ ሚና እንዳለው አመላክተዋል፡፡

ምክክሩ ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያውያን መመራቱን በማድነቅ ፤ የአፍሪካ ሕብረትም አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል፡፡

ሰላምን እና ልማትን ዘላቂ ለማድግ እንደግፋለን ሲሉ የጠቀሱት አምባሳደሩ ፣ ከአጀንዳ 2063 ጋር ተጣጥመው እንዲቀጥሉም ሙሉ በሙሉ ሕብረቱ እገዛ ያደርጋል ብለዋል፡፡

በጉባዔው ላይ ከመላው ኢትዮጵያ የተውጣጡ ከ4 ሺህ በላይ ተሳፊዎች ተገኝተዋል፡፡

ዮሐንስ ደርበው

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review