ባለሥልጣኑ ሚዲያዎች ለወል ትርክትና ለሀገር ግንባታ በኃላፊነት እንዲሰሩ የሚያደርገውን አሰራር አጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል

You are currently viewing ባለሥልጣኑ ሚዲያዎች ለወል ትርክትና ለሀገር ግንባታ በኃላፊነት እንዲሰሩ የሚያደርገውን አሰራር አጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል

AMN-ጥቅምት 18/2019 ዓ.ም

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ሚዲያዎች ለወል ትርክት መጠናከር፣ ለሀገር ግንባታና እድገት እንዲሁም ለብሔራዊ ጥቅም መረጋገጥ በኃላፊነት፣ መርህንና ሙያዊ ሥነ-ምግባርን ባከበረ መልኩ ተግባራቸውን እንዲያከናውኑ የሚያደርግበትን አሰራር አጠናክሮ ማስቀጠል እንዳለበት ተገለጸ።

የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጄኔራል እና የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ቦርድ ሰብሳቢ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ይህን የገለጹት፣ የባለሥልጣኑ ሥራ አመራር ቦርድ የተቋሙን የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የሥራ አፈጻጸም በገመገመበት ወቅት ነው።

በግምገማው ወቅት አምባሳደር ሬድዋን እንደገለጹት፤ ሚዲያዎች ሕግንና ሙያዊ ሥነ-ምግባርን አክብረው እንዲሠሩ ከሚደረገው ክትትልና ቁጥጥር ጎን ለጎን ባለሥልጣኑ ባለፉት ወራት የገነባው ውስጣዊ አቅም፣ መገናኛ ብዙኃን የይዘት ጥራታቸውን እንዲያስጠብቁ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ ይገኛል።

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኃይማኖት ዘለቀ በበኩላቸው፤ ባለሥልጣኑ በአዋጅ የተሰጠውን ተግባርና ኃላፊነት መሠረት በማድረግ፣ የሚዲያ ዘርፉን እድገት በሚመጥን ደረጃ የክትትልና ድጋፍ፣ የአቅም ግንባታ እንዲሁም የቁጥጥር ሥራዎችን ማከናወኑን አብራርተዋል።

በመጨረሻም የሥራ አመራር ቦርዱ ሰብሳቢና አባላት በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነውንና በባለሥልጣኑ ሕንፃ ውስጥ ተገንብቶ ለምረቃ ዝግጁ የሆነውን «የኢትዮጵያ የሚዲያ ልኅቀት ማዕከል» አጠቃላይ ገጽታ መጎብኘታቸውን የባለስልጣኑ መረጃ ያመላክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review