AMN- ጥቅምት 26/2019 ዓ.ም
የሁለተኛው የአፍሪካ ፖለቲካ ፓርቲዎች ጉባኤ አካል የሆነው የአፍሪካ ሴቶች ፖለቲካ አመራሮችና የአፍሪካ ወጣቶች በፖለቲካ ፎረም ጉባኤ ተሳታፊዎች በአዲስ አበባ መሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎትን ጎብኝተዋል።
በመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት ጉብኝታቸውም ፣ ስለማዕከሉ ሰፋ ያለ ማብራሪያና ገለፃ ተደርጎላቸዋል።
በተለይም ተንቀሳቃሽ መሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት የመንግስት የሚሰጣቸውን አገልግሎት ቀልጣፋና ዘመናዊ በማድረግ ኢትዮጵያ በዲጂታል አገልግሎት የሄደችበትን ርቀት ማሳየት ተችሏል።
በታምራት ቢሻው