ብልጽግና ፓርቲ የገባውን ቃልና ዕቅዱን በጥራትና በፍጥነት የመፈጸም ብቃቱ ለሌሎች ዓርአያ የሚሆን ነው

You are currently viewing ብልጽግና ፓርቲ የገባውን ቃልና ዕቅዱን በጥራትና በፍጥነት የመፈጸም ብቃቱ ለሌሎች ዓርአያ የሚሆን ነው

AMN- ጥቅምት 26/2019 ዓ.ም

ብልጽግና ፓርቲ የገባውን ቃልና ዕቅዱን በጥራትና በፍጥነት የመፈጸም ብቃቱ ለሌሎች ዓርአያ የሚሆን ነው ሲሉ የአፍሪካ ፖለቲካ ፓርቲዎች ጉባኤ ተሳታፊዎች ገልጹ፡፡

የ2ኛው የአፍሪካ ፖለቲካ ፓርቲዎች ጉባኤ አካል የሆነው የአፍሪካ ሴቶች ፖለቲካ አመራሮችና የአፍሪካ ወጣቶች በፖለቲካ ፎረም ጉባኤ ተሳታፊዎች ከቀጨኔ-ጊዮን-ባምቢስ እስከ ሰላም መንገድ፣ የወንዝ ዳርቻ ልማትን ጎብኝተዋል።

በጉብኝታቸው ወንዙ እና የወንዝ ዳርቻው ከዚህ ቀደም የነበረውን ገፅታና በወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክት እንዴት መለወጥ እንደተቻለ ገለፃ ተደርጎላቸዋል።

በወንዝ ዳርቻው ተዘዋውረው ቅኝት ያደረጉት የጉባኤ ተሳታፊዎች በተከናወነው ልማት መደነቃቸውን ገልጸዋል።

በተለይም ፕሮጀክቱ በተጀመረ አጭር ጊዜ ውስጥ የተጠናቀቀበት መንገድ ብልጽግና ፓርቲ እንደመንግስት የገባውን ቃልና ዕቅድን በጥራትና በፍጥነት የመፈጸም ብቃቱ ዓርአያ የሚሆን ተግባር መሆኑን ተናግረዋል።

በታምራት ቢሻው

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review