በአንድ ጊዜ 35 ሺህ እንግዶችን ተቀብላ በጨዋነትና በስኬት ያስተናገደችው አዲስ አበባ 80ሺህ ታዳሚዎችን ለመቀበል እየተዘጋጀች ነዉ

You are currently viewing በአንድ ጊዜ 35 ሺህ እንግዶችን ተቀብላ በጨዋነትና በስኬት ያስተናገደችው አዲስ አበባ 80ሺህ ታዳሚዎችን ለመቀበል እየተዘጋጀች ነዉ

AMN – ኅዳር 19/2019 ዓ.ም

አዲስ አበባ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በተለያዩ የከተማ ልማት ስራዎች ያከናወነቻቸው ተግባራት ከአፍሪካ አልፎ ለተቀረው ዓለም ምሳሌ መሆን ችለዋል፡፡

የተገኙት ስኬቶች በመደመር እሳቤ የተቃኙ፣ በአዲስ የስራ ባህል የተደገፉ፣ ህዝብን ያሳተፉ፣ ፍጥነት እና ፈጠራ የታከለባቸው መሆኑ ደግሞ ልዩ ያደርጋቸዋል፡፡

በኮሪደርና ወንዝ ዳርቻ ልማት፣ በአረንጓዴ ልማትና በአየር ንብረት ለውጥ መከላከል፣ በኮንፈረንስ ቱሪዝም፣ በስፖርት፣ በአገልግሎት፣ በህጻናት አስተዳደግና እንክብካቤ፣ በጤና እና ሌሎች ዘርፎች የተገኙት ውጤቶች በአመራሩና በከተማው ነዋሪዎች ትብብርና አንድነት የተሰሩ ናቸው፡፡

አፍሪካን ጨምሮ የተለያዩ ሀገራት ከተሞችም በመደመር እሳቤ የተሰሩትን እነዚህን እና ሌሎች ተሞክሮዎችን አዲስ አበባ በመምጣት ጭምር እየተጋሩት ይገኛሉ፡፡

የቱሪስቶች መዳረሻና መቆያ የሆነችው አዲስ አበባ፣ በንግድ፣ በኢንቨስትመንት፣ በኢንዱስትሪው እና በሌሎች ዘርፎችም የበርካታ አህጉር እና ዓለም አቀፍ ባለሃብቶችን ቀልብ በመሳብ ላይ ትገኛለች፡፡

መዲናዋ በልማት ብቻ ሳይሆን፣ በጸጥታና ደህንነትም ቢሆን በአፍሪካና በዓለም ላይ ፍጹም ሰላማዊ ከሚባሉ ከተሞች ቀዳሚዋ ነች፡፡

እንግዳ ተቀባይነትና አክባሪነት፣ አብሮነትና ወንድማማችነት የሁሉም ኢትዮጵያዊያን መገለጫ ሲሆኑ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎችም ከዚሁ ከኢትዮጵያዊነት እሴት በተቀዳ ባህል እንግዶችን በመቀበልና በማስተናገድ ልዩ ተሞክሮ አላቸው፡፡

ለቱሪዝም፣ ለአህጉር እና ዓለም አቀፍ ጉበዔዎች ወደ መዲናዋ የሚመጡ እንግዶችን ፍጹም ጨዋነት በሞላበት መንፈስ በመቀበልና በማስተናገድ የሀገርን መልካም ገጽታ በመገንባት ላይ ይገኛሉ፡፡

መዲናዋ ዛሬ ላይ ከሺዎች አልፋ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ታዳሚዎችን መቀበልና ማስተናገድ የጀመረች ሲሆን፣ ሰሞኑን ብቻ ከ100 በላይ ሀገራት የተውጣጡ ከ35 ሺህ በላይ ተሳታፊዎች የታደሙበትን ዓለም አቀፍ የህብረተሰብ ጤና ጉባዔን በስኬት አስተናግዳለች።

ከዚሁ ጎን ለጎን የ2026 የአፍሪካ የንግድ ልማት ፎረም እና ዓለም አቀፍ የጥራጥሬና ቅባት እህሎች ጉባዔን በማስተናገድ ላይ የምትገኝ ሲሆን፣ በእነዚህ ጉባዔዎች ላይም በሺዎች የሚቆጠሩ የውጭ ሀገራት ዜጎች ታድመዋል፡፡

ከእነዚህ ትላልቅ አህጉር እና ዓለም አቀፍ ጉባዔዎች ባሻገር፣ ሌሎች መሰል ጉባዔዎችም በየቀኑ በመዲናዋ ይካሄዳሉ፡፡

እነዚህ ጉባዔዎች በስኬት እና በድምቀት መካሄዳቸው ለከተማዋ ዋንኛ የኢኮኖሚ ምንጭ ከመሆናቸውም በላይ፣ የሀገርን ገጽታም የሚገነቡ ናቸው፡፡

አዲስ አበባ አህጉርና ዓለም አቀፍ ጉባዔዎችን የማስተናገድ አቅሟን እና ልምዷን በእጅጉ በማሳደግ ላይ ስትሆን፣ በቀጣዩ ዓመትም ከ80 ሺህ በላይ እንግዶች የሚታደሙበትን 32ኛውን ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባዔን በስኬት ለማስተናገድ በዝግጅት ላይ ትገኛለች።

በወንድማገኝ አሰፋ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review