-በአፋር ክልል በጤናው ዘርፍ ቀደም ሲል የነበረውን መከላከል ላይ ያተኮረ እንቅስቃሴ አሁን ህክምናም ተጨምሮበት አመርቂ ውጤቶች ተመዝግበዋል፤
-በክልሉ ከሦስት ዓመት በፊት ሦስት ሆስፒታሎች ከነበሩበት አሁን የሆስፒታሎች ቁጥር ጨምሯል፣ በጤና ጣቢያ ደረጃ የነበሩ ማስፋፊያ ተደርጎላቸው ወደ ሆስፒታል ደረጃ እንዲያድጉም ተሰርቷል፤
-የመድሃኒት፣ የጤና፣ የአምቡላንስ፣ የጤና ኬላ እና የጤና ጣቢያ ተደራሽነት በየአካባቢው ሽፋኑን ፊት ከነበረው የማሳደግ እና የማዳረስ ሥራ ተሰርቷል፤
-በጤናው ዘርፍ ከተሰራው የተደራሽነት ሥራ ባለፈ በጤና ቁሳቁስ አቅርቦት እና የአገልግሎት ጥራት ላይም ሰፊ ስራ ተሰርቷል፤
-በጤናው ዘርፍ በጣም አመርቂ ውጤት የተገኘበት ሌላኛው ጉዳይ የጤና መድህን አገልግሎት ሲሆን፣ ወረዳዎችን አቅፎ ወደተግባር ከመግባት አኳያ በልዩ ትኩረት በመሰራቱ የክልሉን ማህበረሰብ ተጠቃሚ ከማድረግ አንፃር ይበል የሚያሰኝ ውጤት ሊመዘገብበት ችሏል፤
-የትምህርት ጥራትን በማረጋገጥ ረገድ የሚቀሩ ጉዳዮች ቢኖሩም፤ በመምህራን፣ በተማሪዎች፣ በወላጆች እና በአጠቃላይ በትምህርት ከባቢ በተሰሩ የማሻሻያ ሥራዎች አበረታች ውጤት ተመዝግቧል፤
AMN- ጥር 21/2017 ዓ.ም