AMN-የካቲት 12/2017 ዓ.ም
በፈረንጆዎቹ ሚሊኒየም የተወለደው ብራዚላዊው አንቶኒዮ ማትዮሰ ዶ ሳንቶሰ በሳውፓሎ እና አያክሰ ድንቅ ጊዜ ያሳለፈ ሲሆን አሰገራሚ የኳስ ችሎታውንም አሳይቷል።
አንቶኒዮ እ.ኤ.አ. በ2022 ለ5 አመታት በማንቸሰተር ዩናይትድ ለመቆየት በ95 ሚሊዮን ዶላር ለመዘዋወር ፈረመ።
በክለቡ የነበረው ቆይታ ያሰበውን ያህል አሰደሳች አልነበረም ፤ በያዝነው አመት እንኳን በ14 ጨዋታዎች 1 ግብ ብቻ ነው ያሰቆጠረው።
ክለቡ ማንቸሰተር ዩናይትድም ከአንቶኒዮ ሊያገመኝ ያቀደው ባለመሳካቱ በሰፔን ላሊጋ ለሚጫወተው ሪያል ቤትሰ በውሰት አሳልፎ ሰጥቶታል።
አንቶኒዮም ለሪያል ቤትስ በተሰለፈባቸው 4 ጨዋታዎች 3 ግብ ማሰቆጠር የቻለ ሲሆን ከውጤቱ በኋላ ዛሬ በድጋሚ እራሴን አግኝቼዋለሁ ፣ ደስተኛም ነኝ ብሏል ፡፡