አርባ ምንጭ፤ የልማት ምንጭነቷ እየጎመራ ቀጥሏል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

You are currently viewing አርባ ምንጭ፤ የልማት ምንጭነቷ እየጎመራ ቀጥሏል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

AMN – ሰኔ 26/2018 ዓ.ም

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአርባ ምንጭ ከተማ በ52 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያረፈውን ዘመናዊ የኩሪፍቱ ሪዞርት እና ስፓ በዛሬው ዕለት መጎብኘታቸውን አስታወቁ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፣ አርባ ምንጭ፤ የልማት ምንጭነቷ እየጎመራ ቀጥሏል በማለት የከተማዋን ወቅታዊ የዕድገት ጉዞ አውስተዋል።

ይህ ግዙፍ የቱሪዝም ፕሮጀክት 53 ዘመናዊና ቅንጡ ቪላዎችን ያካተተ ሲሆን፣ ለከተማዋና ለአካባቢው ነዋሪዎች ሰፊ የኢኮኖሚ መነቃቃትን ይዞ መጥቷል።

ሪዞርቱ ሙሉ በሙሉ ወደ ሥራ ሲገባ ከ300 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ቋሚ የሥራ ዕድል እንደሚፈጥር ተገልጿል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በመልዕክታቸው፣ የዚህ ዓይነቱ ግዙፍ ኢንቨስትመንት መፈጠር መንግሥት የዘረጋቸውን መሠረተ ልማቶች ተከትሎ የመጣ ውጤት ነው።

መሰል ኢንቨስትመንቶች የመደመር መንግሥት የገነባቸውን መሠረተ ልማቶች ተከትሎ፣ የግሉ ዘርፍ ማበርከት የሚችለውን ከፍተኛ አስተዋጽኦ በግልጽ የሚያሳይ ነው ብለዋል፡፡

የሀገሪቱን የቱሪዝም አቅም ወደ ላቀ ምዕራፍ ለማሸጋገር መሰል ታላላቅ ፕሮጀክቶች ያላቸው ሚና ከፍተኛ መሆኑን የጠቆሙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ የሀገር ውስጥና የውጭ ባለሀብቶች ይህንን ምቹ ሁኔታ በመጠቀም በኢትዮጵያ በስፋት እንዲሰማሩና መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review