ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ በኢትዮጵያ ከቻይና አምባሳደር ጋር ተወያዩ

You are currently viewing ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ በኢትዮጵያ ከቻይና አምባሳደር ጋር ተወያዩ

AMN – የካቲት 25/2017 ዓ.ም

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ቼን ሀይን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

በውይይቱ ላይ በኢትዮጵያ እና ቻይና መካከል በርካታ የከፍተኛ ልዑካን የጉብኝት ልውውጥ መደረጉ፣ በሁሉም ዘርፎች ያለውን ግንኙነት የበለጠ እንዲጠናከር እና ውጤታማ እንዲሆን እንዳደረገው ተነስቷል።

ዶ/ር ጌዲዮን፣ ለአምባሳደሩ በአፍሪካ ቀንድ እና በአፍሪካ ስላሉ የሰላም እና ጸጥታ ሁኔታዎች ዙሪያ ገለጻ አድርገውላቸዋል።

አምባሳደር ቼን ሀይ በበኩላቸው፣ ቻይና ኢትዮጵያ ለቀጣናው ሰላም እና መረጋጋት ለምታደርገው ጥረት እንደምትደግፍ ገልጸዋል።

አምባሳደሩ በቻይና አፍሪካ ትብብር ፎረም(ፎካክ) ላይ የተወሰኑ ውሳኔዎች ወደ ተግባር እንዲገቡ አገራቸው የተለያዩ ሥራዎችን እያከናወነች መሆኗን መግለፃቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ እና አምባሳደር ቼን ሀይ በዓለም አቀፍ የጋራ ጉዳዮች ዙሪያም የሀሳብ ልውውጥ ማድረጋቸው ተመላክቷል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review