“ወንዝን የበከሉ ድርጅቶች እና ግለሰቦችን ስምንት ሚሊየን ስምንት መቶ አስራ አምስት ሺህ ብር ተቀጡ”-ባለስልጣኑ

You are currently viewing “ወንዝን የበከሉ ድርጅቶች እና ግለሰቦችን ስምንት ሚሊየን ስምንት መቶ አስራ አምስት ሺህ ብር ተቀጡ”-ባለስልጣኑ

AMN-መጋቢት 09/07/2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣ ከአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ጋር በመተባበር ወንዞችና የወንዞች ዳርቻ የበከሉ ድርጅቶችና ግለሰቦችን በዛሬው እለትም በደንብ ቁጥር 180/2017 መሰረት 8,815,000/ ስምንት ሚሊየን ስምንት መቶ አስራ አምስት ሺህ/ ብር የገንዘብ ቅጣት በመቅጣት አስተዳደራዊ እርምጃ መውሰዱን አስታወቀ፡፡

ባለስልጣኑ በዛሬው እለት በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ 2,250,000 ብር፤በየካ ክፍለ ከተማ 1,800,000 ብር ፤በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ 1,415,000 ብር፤በለሚ ኩራ ክ/ከተማ 1,300,000 ብር ቅጣት ተቀጥተዋል።

በተጨማሪ በቦሌ ክፍለ ከተማ 1,150,000 ብር ፤በቂርቆስ ክፍለ ከተማ 700,000 ብር እና በልደታ ክ/ከተማ 200,000 ብር በመቅጣት ለመንግስት ገቢ ተደርጓል።

በአጠቃላይ በዛሬው እለት 26 ድርጅት እና 5 ግለሰቦች በድምሩ 8,815,000/ ስምንት ሚሊየን ስምንት መቶ አስራ አምስት ሺህ/ብር በመቅጣት አስተዳደራዊ እርምጃ ወስዷል።

ባለስልጣኑ ወንወዞችና የወንዞች ዳርቻ በሚበክሉ ድርጅቶችና ግለሰቦች የሚወስደውን እርምጃ አጠናክሮ አንደሚቀጥል ማስታወቁን ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review