የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ተልዕኮውን በብቃት ከመወጣት ባለፈ ማህበራዊ ኃላፊነቱን እያጠናከረ ነው

You are currently viewing የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ተልዕኮውን በብቃት ከመወጣት ባለፈ ማህበራዊ ኃላፊነቱን እያጠናከረ ነው

AMN- ነሐሴ 9/2018 ዓ.ም

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ተልዕኮውን በብቃት ከመወጣት ባለፈ ማህበራዊ ኃላፊነቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ሰላማዊት ዳዊት ገለጹ።

የአገልግሎቱ አመራርና ሠራተኞች በ2018 የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት መርሃ ግብር በጉለሌ ክፍለ ከተማ ለአንድ ሺህ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍና የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር አካሂደዋል።

የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ሰላማዊት ዳዊት በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ ባለፉት ሰባት ዓመታት የክረምት ወቅት የበጎ ፈቃድ ሥራዎች ባህል እየሆኑ መጥተዋል።

በዚህም በኢትዮጵያ እርስበርስ የመተባበር፣ የመረዳዳትና አንዱ ለአንዱ የመድረስ ባህል እንዲዳብር ትልቅ አስተዋፅኦ ማበርከቱን ገልጸዋል። ከችግኝ ተከላ ጋር በተያያዘም በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የተተከሉት ችግኞች የምግብ ዋስትና እያረጋገጡ እንደሚገኙ ተናግረዋል።

አገልግሎቱም ባለፉት ዓመታት በበጎ ፈቃድ ተግባራት ላይ ሲሳተፍ መቆየቱን አንስተዋል። ተቋማቸው በጉለሌ ክፍለ ከተማ እንጦጦ ፓርክ ለአንድ ሺህ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጉን ተናግረዋል።

በሌላ በኩል የአገልግሎቱ አመራርና ሠራተኞች በእንጦጦ ፓርክ ችግኝ በመትከል የአረንጓዴ ዐሻራቸውን አኑረዋል፡፡

በዚህም ለነገ ሀገር ተረካቢ ተማሪዎች በየዓመቱ የሚያደርገው የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍና የተተከሉ ችግኞችን የመከታተል ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል መገለጹን ኢዜአ ዘግቧል።

ድጋፍ የተደረገላቸው ተማሪዎች በበኩላቸው በተደረገላቸው የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review