AMN- ነሐሴ 9/2018 ዓ.ም

በአሜሪካ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ብናልፍ አንዱአለም ከአሜሪካ የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፍራንክ ጋርሽያ ጋር ውይይት አካሂደዋል።
በውይይታቸውም በተለያዩ ወቅታዊ ሀገራዊ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ውጤታማ ምክክር አድርገዋል።
በቀጣናው አካባቢ እየተስተዋሉ ያሉ ተግዳሮቶችን ለመፍታት በሚከናወኑ የትብብር መስኮች በጋራ መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያም ሰፊ ምክክር አካሂደዋል።
ወሳኝ የሆነውን የማዕድን ዘርፍ ጨምሮ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የኢኮኖሚ ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር እና ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር በሚያስችሉ መንገዶች ላይ በጋራ መስራት የሚገባ መሆኑን አፅኖት ሰጥተው መምከራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።