በድሬዳዋ የእስልምና ኃይማኖት ተከታዮች ከስግደት ለሚመለሱ ክርስቲያን ምዕመናን ማዕድ አጋሩ

You are currently viewing በድሬዳዋ የእስልምና ኃይማኖት ተከታዮች ከስግደት ለሚመለሱ ክርስቲያን ምዕመናን ማዕድ አጋሩ

AMN – ሚያዝያ 10/2017

በድሬዳዋ የእስልምና ኃይማኖት ተከታዮች ከስግደት ለሚመለሱ የክርስትና እህት ወንድሞቻቸው ማዕድ አጋሩ።

የስቅለት በዓል ዛሬ ከማለዳው ጀምሮ በድሬዳዋ በሚገኙ የክርስትና ኃይማኖት ተከታዮች ዘንድ በስግደት፣ በዝማሬ፣ በፀሎት እና በንስሃ ሲከበር ውሏል።

የእስልምና ኃይማኖት አባቶችና ተከታዮች በየአብያተ ክርስቲያናቱ ደጃፎች ከስግደት ለሚመለሱ የክርስትና እህት ወንድሞቻቸው ማዕድ በማጋራት አብሮነታቸውን አሳይተዋል።

በማዕድ ማቋደሱ ስነስርዓት ላይ በድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር የተመራና የአስተዳደሩን ካቢኔ አባላት ያካተተው ቡድን ተሳታፊ መሆናቸውም ታውቋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review