AMN – ኅዳር 8/2019 ዓ.ም
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የCOP32 ተመራጭ ፕሬዚዳንት ጌዲዎን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከዓለም አቀፍ የዱር እንስሳት ጥበቃ ድርጅት (World Wildlife Fund) ዓለም አቀፍ የአየር ንብረትና ኢነርጂ ዳይሬክተር እንዲሁም የCOP20 የቀድሞ ፕሬዝዳንት ከሆኑት ከማኑኤል ፑልጋር-ቪዳል ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አካሄዱ።
በውይይታቸው ወቅት አቶ ማኑኤል ፑልጋር-ቪዳል ጌዲዎን (ዶ/ር) ለCOP32 ፕሬዚዳንትነት በመመረጣቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልጸው፣ ድርጅታቸው ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን አጋርነት አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።
ሁለቱ ወገኖች አክለውም፣ የCOP31 ጉባኤ የተሳካ ውጤት እንዲኖረው በጋራ ለመሥራት እና በዚያ የሚገኙ ውጤቶች ወደ አዲስ አበባ በሚያመራው የCOP32 ጉዞ ላይ ቀጣይነት እንዲኖራቸው አጽንኦት ሰጥተው ተወያይተዋል።