ሲቪል ማህበራት ለሰላምና እድገት የሚጠበቅባቸውን ሚና በአግባቡ እንዲወጡ ተጠየቀ

You are currently viewing ሲቪል ማህበራት ለሰላምና እድገት የሚጠበቅባቸውን ሚና በአግባቡ እንዲወጡ ተጠየቀ

AMN-ግንቦት 24/2017 ዓ.ም

“ጠንካራ ሲቪል ማህበራት ለጠንካራ ሃገረ መንግስት ግንባታ” በሚል መሪ ሃሳብ ከተማ አቀፍ የውይይት መድረክ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡

መርሐግብሩ ጅማሮውን ያደረገው በክፍለ ከተማው የተከናወኑ የልማት ስራዎችን በመጎብኘት ነው።

መድረኩን በንግግር የከፈቱት የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አለማየሁ ሚጀና ፤ የአዲስ አበባ ዘርፈ ብዙ እድገት በቀላሉ የመጣ አለመሆኑን አንስተዋል። በመሆኑም እድገቱ ቀጣይነት ይኖረው ዘንድ ሲቪል ማህበራትን አካታች ማድረግ እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።

ሲቪል ማህበራት ለሰላምና እድገት ከፍተኛ ድርሻ እንዳላቸው የገለፁት ዋና ስራ አስፈፃሚው ይህንን የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት በመወጣት ረገድ እየሰሩ ያሉትን ስራ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል።

ማህበራቱ በበኩላቸው ህዝብን አንድ የሚያደርግ ገዢ ትርክት የመገንባት ሃላፊነት እንዳለባቸው በመድረኩ አፅንዖት ተሰጥቷል።

በመቅደስ ደምስ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review