የኢትዮጵያን የባሕር በር የማግኘት ጥያቄ ዓለም አቀፍ አጀንዳ ማድረግ ያስቻለ ስኬታማ የዲፕሎማሲ ስራ መሰራቱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ(ዶ/ር) ገለጹ

You are currently viewing የኢትዮጵያን የባሕር በር የማግኘት ጥያቄ ዓለም አቀፍ አጀንዳ ማድረግ ያስቻለ ስኬታማ የዲፕሎማሲ ስራ መሰራቱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ(ዶ/ር) ገለጹ

AMN ግንቦት 28/2017

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ(ዶ/ር) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 34ኛ መደበኛ ስብሰባው ከምክር ቤቱ አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

የምክር ቤቱ አባላትም የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ለማስጠበቅ በዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ፣ ከጎረቤት ሀገራት ጋር ስላለው ወዳጅነት፣ የባሕር በር ጥያቄ እና ድንበር ዘለል ወንጀሎችን ለመከላከል እየተደረጉ የሚገኙ የትብብር ስራዎችን የተመለከቱ ጥያቄዎችን አንስተዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ(ዶ/ር) በምላሻቸው፥ የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲ የጎረቤት ሀገራትን የሚያስቀድም ስትራቴጂና መርህ የሚከተል ነው ብለዋል።

በዚህም ከጎረቤት ሀገራት ጋር በመሰረተ ልማት ትስስር፣ ንግድና ኢንቨስትመንት፣ በጋራ ሰላምና ደኅንነት ዲፕሎማሲ ስኬታማ የትብብር ስራ እየተከናወነ መሆኑን አብራርተዋል።

በዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲም ባለፉት ዘጠኝ ወራት ብቻ በአፍሪካ ሀገራትና በመካከለኛው ምስራቅ በአስቸጋሪ ሁኔታ ላይ የነበሩ ከ92 ሺህ በላይ ዜጎችን ወደ ሀገራቸው መመለስ እንደተቻለ አስረድተዋል።

የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅምና ፍላጎት ለማስጠበቅም ከቀጣናዊ ኃይሎችና ዓለም አቀፍ አጋሮች ጋር በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ ሰላምና መረጋጋት እንዲረጋገጥ ለቀጣናው ኢኮኖሚ ትስስር መጠናከር ወሳኝ ሚና የምትጫወት ሀገር ስለመሆኗ በተለያዩ አለም አቀፍ መድረኮች እየተረጋገጠ ስለመሆኑም አንስተዋል፡፡

የኢትዮጵያን የባሕር በር የማግኘት ጥያቄ ዓለም አቀፍ አጀንዳ ማድረግ ያስቻለ ስኬታማ የዲፕሎማሲ ስራ መሰራቱንም ሚኒስትሩ አስታውቀዋል።

የባህር በር ጥያቄን ለማሳካት የተጀመረው ዲፕሎማሲያዊ አካሄድ እውን እስኪሆን ድረስ በዓለም አቀፍ ህጎች እና በሰጥቶ መቀበል መርህ እንደሚሰራ ማመላታቸዉን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review