የግንቦት ወር በዓለም ሁለተኛው ሞቃታማ ወር ሆኖ ተመዘገበ

You are currently viewing የግንቦት ወር በዓለም ሁለተኛው ሞቃታማ ወር ሆኖ ተመዘገበ

AMN- ሰኔ 4/2017 ዓ.ም

የፈረንጆቹ 2025 የግንቦት ወር በዓለም ዙሪያ በታሪክ ከተመዘገቡት ሁሉ እጅግ ከፍተኛ ሙቀት ያስተናገደ ሁለተኛው ወር ሆኖ መመዝገቡን የአውሮፓ ሳይንቲስቶች ገልጸዋል።

በወሩ በመካከለኛው ምሥራቅ፣ በምዕራብ እስያ፣ በሰሜን ምሥራቅ ሩሲያ እና በሰሜናዊ ካናዳ ከፍተኛ የሙቀት መጠን መጨመሩ ተነግሯል።

የሙቀት መጠን መመዝገብ ከጀመረ ጊዜ አንስቶ፣ ዓለም በግንቦት ወር ሁለተኛው እጅግ ከፍተኛ ሙቀት የተመዘገበበት ወር አስተናግዳለች ሲል የኮፐርኒከስ የአየር ንብረት ለውጥ አገልግሎት በወርሃዊ የአየር ሁኔታ እትሙ አስታውቋል፡፡

አገልግሎቱ እንዳስታወቀው ከሆነ፣ ባለፈው ወር በዓለም ዙሪያ ያለው የሙቀት መጠን ከቅድመ ኢንዱስትሪ ከ1850 እስከ 1900 ከነበሩት ዓመታት ጋር ሲነጻጸር በአማካይ 1.4 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ ከፍ ብሏል።

በወንድማገኝ አሰፋ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review