ኢራን በአፀፋዊ ጥቃት 100 ድሮኖችን በእስራኤል ላይ ሰነዘረች

You are currently viewing ኢራን በአፀፋዊ ጥቃት 100 ድሮኖችን በእስራኤል ላይ ሰነዘረች

AMN – ሰኔ 6/2017 ዓ.ም

እስራኤል ምሽቱን በኢራን የኒውክሌር መሰረተ ልማቶች እና የጦር ሰፈሮችን ኢላማ ያደረገ የአየር ጥቃት መሰንዘሯን ተከትሎ ኢራን አፀፋዊ ምላሽ ሰጥታለች፡፡

በዚህም ኢራን 100 የጦር ድሮኖችን ወደ እስራኤል መሰንዘሯን የቢቢሲ ዘገባ ያመለክታል፡፡

እስራኤል በኢራን የጦር መንደሮች ላይ በከፈተችው ጥቃት የኢራን አብዮታዊ ዘብ አዛዥ እና ሌሎችም ኮማንደሮች መሞታቸውን የእስራኤል መከላከያ ሀይል አስታውቋል፡፡

የኢራን መንግስታዊ የቴሌቭዢን ጣቢያ የቴህራን የመኖሪያ አፓርታማዎችም የጥቃቱ ሰለባ መሆናቸውን እና በዚህም ቁጥራቸው በውል ያልተወቁ ህጻናትን ጨምሮ የንጹሀን ህይወት ማለፉን ገልጿል፡፡

የአፀፋ ጥቃቱ ከሚፈጥረው የፀጥታ ስጋት አኳያ እስራኤል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በእስራኤል አውጃለች፡፡

እስራኤል በኢራን ላይ በወሰደችው ጥቃት አሜሪካ ድጋፍ አድርጋለች ስትል ኢራን የከሰሰች ሲሆን የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ በበኩላቸው የአሜሪካ እጅ የለበትም ሲሉ አስተባብለዋል፡፡

ዓለም አቀፉ ማህበረሰብም በጥቃቱ ዙሪያ ምላሽ መስጠት የጀመረ ሲሆን፣ አውስትራሊያ በበኩሏ በቀጣናው የተባባሰ የጦርነት ድባብ እንዳይኖር ይህ የማንቂያ ደውል ነው ማለቷ ተሰምቷል፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በበኩሉ ሁለቱም ወገኖች ውጥረቱን ከማባባስ እንዲታቀቡ አሳስቧል፡፡

በወርቅነህ አቢዮ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review