AMN – ሐምሌ 14/2018 ዓ.ም
የ8 ዓመቱ ታዳጊ ቃል ተስፋዬ በሻንጋይ የተካሄደውን ዓለም አቀፍ የፊደል አጻጻፍ ውድድር አሸነፈ።
ቃል ተስፋዬ በቻይና ሻንጋይ ከተማ በ 2026 እ.ኤ.አ በተካሄደው የዓለም የፊደል አጻጻፍ ዋንጫ እና የእስያ ዋንጫ ውድድር ላይ ታላቅ ድል በማስመዝገብ የኢትዮጵያን ስም ከፍ አድርጓል።
ቃል ተስፋዬ ኢትዮጵያን በመወከል የእስያ የፊደል አጻጻፍ ዋንጫ -አንደኛ ደረጃ (በመጀመሪያው ምድብ) ፣ የዓለም የፊደል አጻጻፍ ዋንጫ -የወርቅ ሜዳሊያ (በመጀመሪያው ምድብ) ፣ የዓለም የፊደል አጻጻፍ ዋንጫ -በዓለም አቀፍ ደረጃ 6ኛ ደረጃ (በድብልቅ ምድብ) ድሎች አስመዝግቧል።

በቻይና የኢትዮጵያ ኤምባሲ ስፖንሰር በማመቻቸት እንዲሁም ቀጣይነት ያለው ድጋፍ በማድረግ የዚህን ታዳጊ አቅም በዓለም አቀፍ ደረጃ እንዲያንጸባርቅ አድርጓል።
ኤምባሲው በማሕራዊ ትስስር ገጹ ባስተላለፈው የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት ፣ ቃል ወደ ፊትም ከዚህ በላይ ስኬቶችን እንደሚያስመዘግብ ያለውን እምነት ገልጿል።
በፍሬሕይወት ብርሃኑ