ከንቲባ አዳነች አቤቤ የቴክኒክና ሞያ ቴክኖሎጂ አውደርዕይ መክፈታቸዉን ገለጹ

You are currently viewing ከንቲባ አዳነች አቤቤ የቴክኒክና ሞያ ቴክኖሎጂ አውደርዕይ መክፈታቸዉን ገለጹ

AMN ሰኔ 07/2017

የአዲስአበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ዛሬ ጠዋት “ብሩህ አዕምሮዎች፣ በክህሎት የበቁ ዜጎች” በሚል መሪ ሀሳብ የተዘጋጀውን የቴክኒክና ሞያ ቴክኖሎጂ አውደርዕይ በይፋ መክፈታቸዉን ገልጸዋል፡፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልእክት “ኢትዮጵያ የምትበለጽገው የራሳችንን የሰው ሀይልና የተፈጥሮ ሀብት አቀናጅቶ በማልማት ነው” በሚል ጽኑ አቋም በሰራናቸው ስራዎች የብልጽግና መሰረት እየተጣለ ይገኛል ብለዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ የቴክኒክና ሞያ ተቋማት ለሀገር ብልፅግና ያላቸውን የማይተካ ሚና በአግባቡ በመገንዘብ ለዘርፉ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ በመስራት አመርቂ ውጤቶችን ማስመዝገብ ጀምሯል።

በከተማ አስተዳደሩ እየተከነወኑ ባሉ የልማት ስራዎች ውስጥ የቴክኒክና ሞያ ተቋማት የእጅ ስራ ውጤት የሆኑ የተለያዩ ተኪ እና ጥራት ያላቸዉ ግብዓቶችን ከማቅረብ ጀምሮ የሰለጠነ የሰዉ ሀይል በማፍራት በበርካታ ስራዎች ላይ አሻራቸውን ማሳረፍ መጀመራቸው የሀገራችን ብልጽግና የሚሳካው በቴክኖሎጂ አመንጪ ኢትዮጵያውያን ለመሆኑ ትልቅ አብነት ነው።

ለዛሬው አውደርዕይ የቀረቡትን የቴክኖሎጂ ስራዎች ላይ የበኩላችሁን አስተዋጽኦ ያበረከታችሁ ሰልጣኞችን፣ አሰልጣኞችን፣ ባለሞያዎችን እና መላውን አመራር አመሰግናለሁ ሲሉ ገልጸዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review