ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዕውን እንዲሆን የዲፕሎማሲ ስራዎች ከፍተኛ ሚና መጫወታቸው ተገለጸ

You are currently viewing ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዕውን እንዲሆን የዲፕሎማሲ ስራዎች ከፍተኛ ሚና መጫወታቸው ተገለጸ
  • Post category:ልማት

AMN- ሰኔ 10/2017 ዓ.ም

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዕውን እንዲሆን የዲፕሎማሲ ስራዎች ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል ሲሉ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር ኢ/ር) ገለጹ፡፡

ኢትዮጵያ የኃይል አቅርቦት እጥረትን ለመፍታት እየገነባች ያለው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የውሃ ፍሰትን መጠን ይቀንሳል በሚል ሀሰተኛ ክስ በማቅረብ ግድቡን ከግብ እንዳታደርስ ከፍተኛ የፕሮፖጋንዳ ስራዎች ሲሰሩባት መቆየቷ የአደባባይ ሀቅ ነው።

ኢትዮጵያ ሁሉንም የተፋሰስ ሀገራት ተጠቃሚ የሚያደርግ መርህ ላይ የተመሰረተ ዲፕሎማሲ እንደምትከተል የገለፁት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ፣ የዲፕሎማሲ ስራው ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት እንድታገኝ አስተዋፅኦ ማድረጉን በተለይ ለአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ተናግረዋል።

ሚኒስትሩ ህዳሴ ግድቡ አልቋል የሚባልበት ደረጃ ላይ መድረሱን በማንሳት የኢትዮጵያ ህዝብ ለግድቡ ግንባታ እስካሁን 23 ቢሊየን ብር ማዋጣቱን ተናግረዋል።

ገንዘብ ከማዋጣት ባሻገር የፀጥታ መዋቅሩም በርካታ ስራዎችን መስራቱንም አክለው ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ ህዝብ ከግድቡ ግንባታ መጀመር አንስቶ ድጋፍ እያደረገ እንደነበር የገለፁት የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር አረጋዊ በርሔ (ዶ/ር) የህዝብ ዲፕሎማሲ ስራዎች ለግድቡ መሳካት አስተዋፅኦ ማድረጉን ተናግረዋል።

ዋና ዳይሬክተሩ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ኢትዮጵያውያን ይችላሉ” የሚለውን ለዓለም ያሳየ መሆኑንም አክለው ገልፀዋል።

ግድቡ ሲጠናቀቅ ኢትዮጵያ የኃይል እጥረት ችግሯን በመፍታት የኢንዱስትሪ ልማቷን ከማፋጠን ባለፈ የተረፈውን የኃይል ምርት በአፍሪካ ቀንድ ለሚገኙ ጎረቤት ሀገራት በማቅረብ፣ የአካባቢውን ኢኮኖሚያዊ ትስስር ያጠናክራል ተብሎ ይጠበቃል።

በኤደን ገብረእግዚአብሔር

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review