ከንቲባ አዳነች አቤቤ አፍሪካዊያን እጅ ለእጅ ተያይዘን ለተሻለ ነገ ከልብ እንስራ ሲሉ ጥሪ አቀረቡ

You are currently viewing ከንቲባ አዳነች አቤቤ አፍሪካዊያን እጅ ለእጅ ተያይዘን ለተሻለ ነገ ከልብ እንስራ ሲሉ ጥሪ አቀረቡ

AMN – ሰኔ 11/2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባስተላለፉት መልእክት አፍሪካዊያን እጅ ለእጅ ተያይዘን ለተሻለ ነገ ከልብ እንስራ ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ዛሬ “በአፍሪካ ጥራት ያለውና አካታች የሆነ የህጻናት እድገትን ለማረጋገጥ የጋራ ትብብርን ማጠናከር” በሚል መሪ ቃል የአፍሪካ የህፃናት ክብካቤ እና ጥበቃን የተመለከተ ኮንፍረንስ በአፍሪካ ህብረት አዳራሽ እየተካሄደ ነዉ።

ኮንፍረንሱ አዲስ አበባ እንዲካሄድ የተመረጠዉ ከተማዋ የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ ስለሆነች ብቻ ሳይሆን አዲስ አበባ ህጻናት በአዕምሮ፣ በአካል እና በስነልቦና የተሟላ ዕድገት እንዲጎናጸፉ ለማስቻል የሰራችዉ የተቀናጀ እና አካታች የቀዳማይ ልጅነት ልማት ፕሮግራም አፍሪካውያን ትምህርት የሚወሰዱበት ውጤታማ ስራ በመሆኑ ጭምር ነው ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገልጸዋል።

እኛም አፍሪካዊያን እጅ ለእጅ ተያይዘን ለተሻለ ነገ ከልብ እንድንሰራ ጥሪ በማቅረብ እስካሁን በከተማችን የሰራናቸዉን ስራዎች ልምድ አጋርተናል ብለዋል።

በመጨረሻም መድረኩን ያዘጋጀውን የአፍሪካ ህብረት የጤና፣ የሰብዓዊ ጉዳዮችና ማህበራዊ ልማት ኮሚሽንን እአመስግነው፤ ኮንፈረንሱን ለመታደም ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የመጣችሁ ሚንስትሮች ፣ የዓለም አቀፍ ተቋማት መሪዎች፣ የዘርፉ ባለሞያዎች እና ተመራማሪዎች በከተማችሁ አዲስ አበባ ያላችሁ ቆይታ ያማረ እና የተሳካ እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ ሲሉ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው አስፍረዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review