ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሕዝብ እና ከግል ሚዲያዎች ከተወጣጡ ባለሞያዎች ጋር መወያየታቸዉን ገለጹ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልእክት ከባለድርሻ አካላት ጋር የሚደረጉ ውይይቶች የመጨረሻው የሆነው ውይይት ዛሬ ከሕዝብ እና የግል ሚዲያዎች ከተወጣጡ ባለሞያዎች ጋር መካሔዱን ገልጸዋል፡፡
በዉይይቱ በኢንደስትሪው ያሉ ልዩ ጉዳዮች እና ተግዳሮቶች መዳሰሳቸዉን ገልጸዋል፡፡
ሚዲያ በኢትዮጵያ የልማት ሥራዎች ውስጥ ሕዝብን በማሳወቅ፣ ውይይትን በማዳበር እና ብሔራዊ የእድገት ርምጃን በመደገፍ ቁልፍ ሚና አላቸው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልእክት አስተላልፈዋል፡፡