የሚዲያና ኮሚኒኬሽን ባለሙያዎች ሀገሪቱ እያከናወነች ያለችውን የልማት እንቅስቃሴዎች ህዝቡ እንዲረዳው እና እንዲደግፈው ከማድረግ ረገድ የበኩላቸውን እንዲወጡ ተጠየቀ

You are currently viewing የሚዲያና ኮሚኒኬሽን ባለሙያዎች ሀገሪቱ እያከናወነች ያለችውን የልማት እንቅስቃሴዎች ህዝቡ እንዲረዳው እና እንዲደግፈው ከማድረግ ረገድ የበኩላቸውን እንዲወጡ ተጠየቀ
  • Post category:ልማት

AMN ሰኔ 17/2017

ባለሞያዎቹ በጅማ እና አካባቢዋ የተሰሩ የልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል።

በአዲስ አበባ የተሰሩት የተለያዩ ተግባራት የከተማዋን የቱሪዝም መዳረሻነት ያጎሉ እና የአፍሪካ መዲናነቷን ይበልጥ ያረጋገጡ ስራዎች መሆናቸውን ጠቅሰዋል።

እያንዳንዱ ስራም ህዝብ ተኮር በመሆኑ ከፍተኛ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን የቀረፉ መሆናቸውን ሀሳባቸውን ለኤ ኤም ኤን የሰጡ ባለሞያዎች ገልፀዋል።

ባለሙያዎቹ በጅማ ከተማ የተገነቡ የኮሪደር ልማት : የአባ ጅፋር ቤተመንግስት : ተመልሶ በማገገም ላይ የሚገኘዉን የቦዬ ሀይቅን ጨምሮ ሌሎች የልማት ስራዎችን እና የተፈጥሮ ሃብቶችን ጎብኝተዋል።

አስተያየት ሰጪዎቹ ከጅማ ከተማ ታሪካዊነት : ካላት የአየር ንብረትና የተፈጥሮ ሃብት እንዲሁም መልካዓ ምድራዊ አቀማመጥ እየተሰሩ ያሉ መሰረተ ልማቶች በቱሪዝም ኮንፈረንስ ረገድ ለጅማ ከተማ መሠረት የሚጥሉ መሆናቸዉን ጠቅሰዋል።

በመንግስት እና በግሉ ዘርፍ ርብርብ እየተሰሩ ያሉ የልማት ስራዎችም አበረታች መሆናቸዉን ተናግረዋል።

የከተማዋ ከንቲባ አቶ ጠሃ ቀመር በበኩላቸው በከተማዋ እየተሰሩ ያሉ የልማት ስራዎች ሰዉ ተኮር መሆናቸውን ገልፀዋል።

በልማት ምክንያት ለተነሱ ከ200 በላይ አባወራዎችም ደረጃውን የጠበቀ ቤት ተገንብቶ መሰጠቱንም ገልፀዋል።

በከተማዋ የልማት እንቅስቃሴ ውስጥ ህዝቡ እያደረገ ላለው ተሳትፎም አመስግነዋል።

በአፈወርቅ አለሙ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review