በኢትዮጵያ ያልተነካ እምቅ አቅም ያለው በኮንስትራክሽኑ ዘርፍ መሆኑ ተገለጸ

You are currently viewing በኢትዮጵያ ያልተነካ እምቅ አቅም ያለው በኮንስትራክሽኑ ዘርፍ መሆኑ ተገለጸ

AMN- ሰኔ 17 ቀን 2017ዓ.ም

የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ በኢትዮጵያ ያልተነካ እምቅ አቅም ያለው በኮንስትራክሽኑ ዘርፍ ላይ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ከዲ ኤም ጂ ኤቨንትስ ከተባለ አለም አቀፍ ተቋም ጋር በመሆን ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል::

በጋራ በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫም የኢትዮጵያ ከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትሯ ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ በኢትዮጵያ ካልተነኩ የስራ ዘርፎች የኮንስትራክሽን ዘርፉ አንዱና ዋናው መሆኑን ገልፀው በኢትዮጵያ 19 በመቶ ለወጣቱ የስራ እድል የፈጠረው ከግብርና በመቀጠል ይኸዉ ዘርፍ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

ከቅርብ ጊዜ ወዲህም መዲናችን አዲስ አበባ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ እየተገነባች እንደምትገኝ አውስተው እንደ ዲ ኤም ጂ የመሳሰሉ አለም አቀፍ ኤቨንት ኦርጋናይዘሮች የሚመርጧት ከተማ ሆናለች ብለዋል::

ዲ ኤም ጂ ኤቨንትም ከሰኔ 19 እስከ ሰኔ 21 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ የሚቆይ በአይነቱ ለየት ያለ በኮንስትራክሽን ላይ ያተኮረ ‘ቢግ ፋይቭ ኮንስትራክት ኢትዮጵያ’ የተሰኘ አውደ ርእይ እና ኤክስፖ በሚሊኒየም አዳራሽ እንደሚያካሂድ ተገልጿል፡፡

በየሺዋስ ዋለ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review