በ90 ሄክታር ቦታ ላይ እየተገነባ የሚገኘው የኢንዱስትሪ ክላስተር የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታ እየተጠናቀቀ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ተናገሩ

You are currently viewing በ90 ሄክታር ቦታ ላይ እየተገነባ የሚገኘው የኢንዱስትሪ ክላስተር የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታ እየተጠናቀቀ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ተናገሩ
  • Post category:ልማት

AMN ሰኔ 18/2017

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ የኢንዱስትሪ ክላስተሩን የግንባታ ሂደት ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።

የከተማው አስተዳደሩ አዲስ አበባን ውብ ጽዱ እና ለኑሮ ምቹ ለማድረግ እየሰራ ካለው ተግባር ጎን ለጎን የስራ እድል ለመፍጠር እና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናግረዋል።

በዚህም የኢንዱስትሪ ክላስተርን ለመገንባት ቦታ በማዘጋጀት በመጀመሪያው ምዕራፍ በ7 ቢሊየን ብር 120 የማምረቻ ሼዶች በመገንባት ላይ ሲሆኑ ለብረታ ብረት፣ ለእንጨት፣ ለፕላስቲክና ኬሚካል ኢንዱስትሪዎች ምርት የሚውሉ 48 ሼዶች ግንባታ ሙሉ በሙሉ መጠናቀቁን እና ለጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪዎች የሚውሉ 72 ሼዶች ደግሞ በመጠናቀቅ ላይ መሆናቸውን ከንቲባ አዳነች አስታውቀዋል።

ክላስተሩ ተጠናቆ ወደ ስራ ሲገባ 20 ሺ ለሚደርሱ ዜጎች የስራ እድል ይፈጥራል ተብሎ የሚጠበቀው የኢንዱስትሪ ክላስተሩ የማምረቻ፣ የምርት ማሳያ፣ መሸጫ እና መዝናኛ ስፍራዎችን ያከተተ መሆኑንም ገልጸዋል።

የኢንዱስትሪ ክላስተሩ በተለያዩ ወቅቶች በዘመናዊ መንገድ ምርትን ለማምረት የሚያስችል ቴክኖሎጂዎችን ያሟላ መብራትና ውሃን መሰል መሰረተ ልማቶች የተሟሉለት መሆኑንም ከንቲባ አዳነች ተናግረዋል።

የከተማ አስተዳደሩ የሚሰሩ እጆችን ለማበረታታት እና በከተማዋ ምርትን በማሳደግ ተኪ ምርቶችን ለማምረት ብሎም ወደ ውጭ ለመላክ ለዘርፉ ትኩረት መስጠቱን የተናገሩት ከንቲባ አዳነች በመስኩ ያለውን የመስሪያ ቦታ ችግር ጥያቄ ለመመለስ በዚህ አመት ብቻ ከ3ሺ በላይ መደበኛ ሼዶች ተገንብተው መተላለፋቸውንና ለመካከለኛ እና ከፍተኛ አመራቾች ደግሞ የኢንዱስትሪ ክላስተሩ መዘጋጀቱን አስታውቀዋል።

በኢንዱስትሪ ክላስተሩ የተገነቡ የመስሪያ ቦታዎች ከሚቀጥለው በጀት አመት ጀምሮ ለአምራቾች መተላለፍ እንደሚጀምሩም ተገልጿል፡፡

በሰብስቤ ባዩ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review