አሜሪካ እና ኢራን ለውይይት እንደሚገናኙ ፕሬዚደንት ትራምፕ አስታወቁ

You are currently viewing አሜሪካ እና ኢራን ለውይይት እንደሚገናኙ ፕሬዚደንት ትራምፕ አስታወቁ

AMN – ሰኔ 18/2017 ዓ.ም

የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አሜሪካ በኢራን የኒውክሌር ጣቢያዎች ላይ የእስራኤልን ጥቃት ከተቀላቀለች በኋላ በኢራን እና በእስራኤል መካከል ያለው ጦርነት በፍጥነት ማብቃቱን ተናግረዋል።

ምንም እንኳን የአሜሪካ ጥቃት የኢራን የኒውክሌር ግስጋሴን በጥቂት ወራት ብቻ እንዳዘገየ የአሜሪካ የስለላ ድርጅት ቢያስታውቅም ትራምፕ ግን የአሜሪካን ጥቃት የሁሉም ሰው ድል ነው ብሎታል።

ትራምፕ በሄግ በተካሄደው የኔቶ ጉባኤ ላይ ንግግር ሲያደርጉ በሚቀጥላው ሳምንት አሜሪካ ከኢራን ጋር ለውይይት እንደሚቀመጡና ውይይቱም ወደ ስምምነት ሊያመራ እንደሚችል አመላክተዋል ሲል ሮይተርስ ዘግቧል።

ኢራን አሁን ሰላም ትፈልጋለች ያሉት ትራምፕ ከዚህ በሗላ የኒውክሌር ፕሮግራሟን እንደገና ለመገንባት እንደማትሞክር ያላቸውን እምነት ገልፀዋል።

እስራኤል ጥቃቱ የኢራንን የኒውክሌር የማበልፀግ ጥረቶች ለብዙ አመታት ወደኋላ እንደሚጎትት ያስታወቀች ቢሆንም የተባበሩት መንግስታት የኒውክሌር ሃላፊ ግን ጉዳቱ በወራት መመዘን የለበትም ብለዋል።

ትክክለኛውን ሁኔታ ለመረዳት እና የረጅም ጊዜ መፍትሄ ለማግኘት ተቆጣጣሪዎችን ወደ ኢራን መመለስ እንደሚያስፈልግም አሳስበዋል።

በሊያት ካሳሁን

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review