ኢትዮጵያውያን ሲተባበሩ ተአምር እንደሚሠሩ ዛሬ ዳግም ታይቷል-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶር)

You are currently viewing ኢትዮጵያውያን ሲተባበሩ ተአምር እንደሚሠሩ ዛሬ ዳግም ታይቷል-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶር)

AMN-ሐምሌ 24/2017 ዓ.ም

ኢትዮጵያውያን ሲተባበሩ ተአምር እንደሚሠሩ ዛሬ ዳግም መታየቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶር) በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት ገልፀዋል።

“በመትከል ማንሠራራት” በሚል መሪ ቃል ፣ በአንድ ቀን 700 ሚልዮን ዛፎችን ለመትከል ያቀድነው ዕቅድ ከታሰበው በላይ ተሳክቷልም ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው።

አመራሮችና ሠራተኞች፣ የግልና የመንግሥት ተቋማት፣ ኤምባሲዎች እና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች፣ ሕጻናት፣ ወጣቶች፣ ጎልማሶች፣ አረጋውያን፣ ወንዶችና ሴቶች ለአረንጓዴ ዐሻራ፣ ዛሬ በማለዳ፣ ከወፎች ቀድመው መውጣታቸውን ያስታወሱት ጠቅላይ ሚኒስተር ዐቢይ “አረንጓዴ ዐሻራ የኢትዮጵያውያን ባህል እየሆነ ነው ፤ የኢትዮጵያን መልክም እየቀየረ ነው፣

የኢትዮጵያን ታሪክም እየቀየረ ነው። የዓለምንም መልክ እየቀየረ ነው” ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አክለውም ይሄንን ተልዕኮ የሚያስተባብሩትን፣ ጥሪያችንን ሰምተው ወጥተው የተከሉትን ሁሉ እናመሰግናለን ብለዋል።

አክለውም ኢትዮጵያውያን ፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያን እና የውጭ ዜጎች በብዛት እና በምልዐት ስላደረጉት ተሳትፎ በኢትዮጵያ ስም አመስግነዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review