ከንቲባ አዳነች አቤቤ በከፍተኛ የአገር ፍቅር ስሜትና ድል አድራጊነት በነቂስ ወደ አደባባይ በመትመም ደስታዉን ለገለፀዉ ብሔራዊ ጀግኖቹን ላመሰገነዉ መላዉ የአዲስ አበባ ነዋሪ በሙሉ ምስጋና አቅርበዋል።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልዕክት ምስጋና ብሔራዊ ድሉን ላከበረዉ ፣ ብሔራዊ ጀግኖቹን ላመሰገነዉ የከተማችን ነዋሪ በሙሉ ሲሉ ገልጸዋል።
ዛሬ ማለዳ በከፍተኛ የአገር ፍቅር ስሜትና ድል አድራጊነት በነቂስ ወደ አደባባይ በመትመም ደስታዉን ለገለፀዉ ብሔራዊ ጀግኖቹን ላመሰገነዉ መላዉ የአዲስ አበባ ነዋሪ በሙሉ ምስጋናዬን አቀርባለዉ !

ፕሬዝዳንት ታዬ አዝቀስላሴ ፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ እና ሌሎችም ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ፣ የሀይማኖት አባቶች ፣ የአገር ሽማግሌዎች ፣ የዲፕሎማሲዉ ማህበረሰብ በተገኙበት መላዉ የከተማችን ነዋሪዎች ከመቀነቱ ፈቶ ፣ ካለዉ ቆርሶ ፣ የኑዛዜዉ አካል አድርጎ ፣ ህፃናት ተማሪዎች ሳይቀሩ የከረሜላ መግዣቸዉን ለቦንድ መግዣ አዉለዉ፣ ብዙ አለም አቀፍ ጫና ዉስጥ በደምና አጥንት መስዋትነት ገንብተዉ ለፍፃሜ ያበቁትን የህዳሴ ግድብ ድል በታላቅ ድምቀት አክብረዋል ።
መላዉ የከተማችን ነዋሪዎች የሌሊት ቁር የዛሬዉ ከባድ ዶፍ ዝናብ ሳይበግራችሁ የዘመናት ፣የትዉልዶች ትግል ዉጤት የሆነዉ ድላችሁን በጋራ አክብራቹሃል ፣ ለዚህ ድል ከነበራችሁ ደጀንነት አንፃር ይገባቹሀል !
ይህ ድል የኢትዮዽያ የመቻል ማሳያ ፣የአይቀሬዉ ብልፅግናችን ማረጋገጫ ብሔራዊ ምልክት ነዉ።
በድጋሚ እንኳን ደስ አለን ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።