በኘሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ የተመራ የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን በ80ኛው የተመድ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ እየተሳተፈ ነው

You are currently viewing በኘሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ የተመራ የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን በ80ኛው የተመድ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ እየተሳተፈ ነው

AMN መስከረም 12/ 2018

በኢፌዴሪ ኘሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ የተመራ የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን በ80 ኛው የተባበሩት መንግስሥታት ድርጅት(የ.ተ.መ.ድ.) ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ተሳትፎ ለማድረግ ኒው ዮርክ ገብቷል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሃደራ አበራን ጨምሮ የተለያዩ ተቋማት ያካተተው የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን በኒውዮርክ ”Better Together” ”ደህናነት በአብሮነት” በሚል መሪ ሀሳብ በሚካሄደው የ.ተ.መ.ድ.80ኛ ጠቅላላ ጉባዔ ተሳትፎውን ጀምሯል።

ኢትዮጵያ በጉባዔው ላይ የራሷን ብሔራዊ ጥቅሞች እና የአፍሪካን ጥቅሞች በሚያስጠብቁ ጉዳዮች ላይ ንቁና ጠንካራ ተሳትፎ ታደርጋለች።

ከዋናው ጉባዔ ተሳትፎ በተጨማሪ በርካታ የሁለትዮሽና የባለብዙ ወገን የጎንዮሽ የውይይት መድረኮች ላይም ኢትዮጵያ የራሷን ብሄራዊ ጥቅሞች ቅድሚያ እየሰጠች ትሳተፋለች።

ዓለም በተለያዩ ሠላምና ፀጥታ ጉዳዮች እየተፈተነች ባለበት ወቅት የሚከበረው የተመድ 80ኛ ዓመት አባል ሀገራት ከመቼውም ጊዜ በላይ አብሮነታቸውን በማጠናከር የተሻለች ዓለም ለመፍጠር መሥራት እንደሚገባቸው መገለጹን ከዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review