ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልእክት የማሌዢያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዳቶ ሴሪ አንዋር ኢብራሂም የመላው ጥቁር ሕዝቦች ኩራት የሆነውን የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጎብኝተዋል ብለዋል፡፡
የማሌዢያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዳቶ ሴሪ አንዋር ኢብራሂም በምድረ ቀደምቷ ኢትዮጵያ ውቧ መዲናችን አዲስ አበባ የሚያደርጉት ቆይታ ፍሬያማ እንዲሆን በራሴና በከተማ አስተዳደሩ ስም እመኛለሁ ሲሉ ገልጸዋል፡፡