ከንቲባ አዳነች አቤቤ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያን በልዩ ድምቀት አስጀመሩ

You are currently viewing ከንቲባ አዳነች አቤቤ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያን በልዩ ድምቀት አስጀመሩ

AMN ህዳር 14/2018

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልእክት ተወዳጁን ፣ ተናፋቂውን እና ባለፉት 25 ዓመታት የከተማችን አንዱ ድምቀት እና አለም አቀፍ መገለጫ የሆነውን ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያን በልዩ ድምቀት አስጀምረናል ብለዋል፡፡

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የዓለም ኮከብ አትሌቶች መለማመጃ ፣ መኖሪያ በሆነችው መዲናችን አዲስ አበባ ፣ ከልጅ እስከ አዋቂ፣ ከፕሮፌሽናል አትሌት እስከ ጤና ቡድኖች፣ ታዋቂ ግለሰቦች እና የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰቡ እየተሳተፈበት፣ እየተዝናናበት፣ ጤናውን እየጠበቀበት፣ ወንድማማችነትን፣ እህትማማችነትንና አብሮነትን እያጠናከረበት 25 የድምቀት ዓመታትን አሳልፏል።

የዚህ ታላቅ ውድድር መስራች የሆነውን ጀግናው አትሌታችንን ሻለቃ ኃይሌ ገ/ሥላሴን፣ እንዲሁም አጠቃላይ የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አመራሮችን ባለሙያዎችን እና አስተባባሪዎችን ለዘመን ተሻጋሪ ሥራችሁ እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እወዳለሁ ብለዋል፡፡

አስተዳደራችን በቀጣይም ይህ ውድድር እንደ ሌሎችም ዓለም አቀፍ የጎዳና ላይ ውድድሮች ይበልጥ ተጠቃሽ እና ተተኪዎችን ጭምር የምናፈራበት እንዲሆን ይበልጡኑ አበክሮ ይሠራል።

ተሳታፊዎች ፣ የፀጥታ አካላት፣ በጎ ፈቃደኞች፣ የሚዲያ ባለሙያዎች እና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት ለውድድሩ ስኬት ለነበራችሁ በጎ አስተዋፅኦ ከልብ አመሰግናለሁ ሲሉ ገልጸዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review