ማርበርግ ቫይረስ ተስፋፍቶ የከፋ ጉዳት እንዳያስከትልና ወረርሽኙን ለመቆጣጠር እየተሠራ ነው

You are currently viewing ማርበርግ ቫይረስ ተስፋፍቶ የከፋ ጉዳት እንዳያስከትልና ወረርሽኙን ለመቆጣጠር እየተሠራ ነው
  • Post category:ጤና

AMN ሕዳር 27/2018

የማርበርግ ቫይረስ በኢትዮጵያ የተወሰኑ አካባቢዎች ከተከሰተ ጀምሮ ተስፋፍቶ የከፋ ጉዳት እንዳያደርስና ወረርሽኙን ለመቆጣጠር ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሠራ መሆኑን ጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

በቫይረሱ የታመሙና ንክኪ ያላቸው በለይቶ ማቆያ ሆነው ምርመራ እየተደረገላቸውና ሕክምና እያገኙ መሆኑን የጤና ሚኒስትር ከፍተኛ አማካሪ ዶክተር አስቻለው ወርቁ ተናግረዋል።

ይህም የሰዎችን ሕይወት ለመታደግ ብሎም ህመሙ ወደ ሌሎች የቤተሰብ አባላት እና ዜጎች ተላልፎ ጉዳት እንዳያደርስ ማስቻሉን ገልጸዋል።

ለጽኑ ህሙማን ሕክምና መስጠት የሚያስችል መድኃኒት ወደ ሀገር ውስጥ በመግባት ላይ መሆኑንም አመላክተዋል።

ቫይረሱ በተገኘባቸው ሀገራት ይሰጥ የነበረ ክትባት ከአሜሪካ መንግሥት በድጋፍ መገኘቱን ገልጸው፤ በቀጣይ ቀናት በቅድሚያ ለጤና ባለሙያዎችና ከፍተኛ ተጋላጭ ቡድኖች እንደሚሰጥ ጠቁመዋል።

ህመሙ እንዳይስፋፋ በመንግሥት በኩል ከሚደረጉ ጥረቶች በተጨማሪ የሕብረተሰቡን ግንዛቤ ማሳደግ የሚያስችሉ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑንም አመላክተዋል።

በዚህም መሠረት በጤና ሚኒስቴር እና በኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ማኅበራዊ ትስስር ገጾች፣ በተለያዩ የብዙኃን መገናኛ አማራጮች ስለቫይረሱ ወቅታዊ መረጃዎች እየቀረቡ መሆኑን ተናግረዋል።

የሚቀርቡ የጥንቃቄ መልዕክቶችን በመከታተልና በመተግበር ሕብረተሰቡ እራሱን ከቫይረሱ መጠበቅ እንዳለበት ማሳሰባቸዉን ኢዜአ ዘግቧል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review