ሲዳማ ባንክ በበጀት ዓመቱ 126 ነጥብ 9 ሚሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ አገኘ

You are currently viewing ሲዳማ ባንክ በበጀት ዓመቱ 126 ነጥብ 9 ሚሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ አገኘ
  • Post category:ቢዝነስ

AMN – ሕዳር 27/2018 ዓ.ም

ሲዳማ ባንክ አ.ማ የባለ አክሲዮኖች 4ኛ መደበኛ እና አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔዉን አካሂዷል፡፡

የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሊቀመንበር አቶ አብርሀም ማርሻሎ ሲዳማ ባንክ ጠቅላላ ሀብቱ 5 ነጥብ 52 ቢሊዮን ብር መድረሱን እና ከአምናዉ ተመሳሳይ ወቅት ሲነፃጸር የ111 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን ገልጸዋል፡፡

ባንኩ ዓለም በዓቀፍ የኢኮኖሚ መዋዠቅ እና በሀገር ዉስጥ በመንግስት በተካሄደዉ መዋቅራዊ ማስተካከያ መደረጉ በጥንካሬ ተወዳዳሪ ነቱን በማሳየቱ በበጀት አመቱ አመርቂ የፋይናንስ ዉጤት ማስመዝገብ ችሏል፡፡

ባንኩ በበጀት ዓመቱ የተጣራ ትርፍ 126 ነጥብ 9 ሚሊዮን ብር ማግኘቱንም የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሊቀመንበር አቶ አብርሀም ማርሻሎ ጨምረዉ ተናግረዋል፡፡

በተጠናቀቀዉ በጀት ዓመት የባንኩ የሀብት ክምችቱ 3 ነጥብ6 ቢሊዮን ብር ማድረስ መቻሉን የገለጹት አቶ አብርሀም ከአለፈዉ አመትጋር ሲነፃፀር በ200 በመቶ ከፍ ያለ መሆኑንም አንስተዋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባስቀመጠዉ አቅጣጫ መሰረት 5ቢሊዮን የተከፈለ ካፒታል ለማድረስ ሁሉም የባንኩ ባለ አክሲዮኖች ተጨማሪ አዳዲስ አክሲዮኖችን እንዲገዙ የቦርዱ ሊቀመንበር አቶ አብርሀም ማርሻሎ ጥሪ አቅርበዋል።

በአልማዝ ሙሉጌታ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review