ከማዕድን ዘርፍ ከ5 ነጥብ 7 ቢሊየን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሬ ተገኘ

AMN- ሐምሌ 30/2018 ዓ.ም

በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት ከማዕድን ዘርፍ ወጪ ንግድ ከ5 ነጥብ 7 ቢሊየን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሬ ተገኝቷል አለ የማዕድን ሚኒስቴር፡፡

የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የ2018 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም እና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ግምገማ እየተካሄደ ነው፡፡

በዚሁ ወቅትም፤ የማዕድን ዘርፍ ከአምስቱ የሀገሪቱ የኢኮኖሚ ምሠሶዎች አንዱ መሆኑን የማዕድን ሚኒስትር ሀብታሙ ተገኝ (ኢ/ር) አስረድተዋል፡፡

በዚህም መሠረት በተሰጠው ልዩ ትኩረት ባለፉት ዓመታት የማዕድን ዘርፉ ዕድገት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን ነው የገለጹት፡፡

ይህን ተከትሎም በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከዘርፉ ከ5 ነጥብ 7 ቢሊየን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሬ ተገኝቷል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review