የኢትዮጵያን የኒውክሌር ኃይል ልማት መርኃ ግብር ማስጀመሪያና የኢትዮጵያ የኒውክሌር ኃይል ኮሚሽን ሥራ ማስጀመሪያ የምክክር መድረክ ለመሳተፍ የመጡት የዓለም አቀፍ አቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሚካኤል ቹዳኮቭ የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጎብኝተዋል፡፡
የኤጀንሲዉ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሚካኤል ቹዳኮቭባዩት ነገር መደሰታቸዉን እና መገረማቸዉን ተናግረዋል፡፡
ኢትዮጵያዊያን ሃገሪቱን ሊወር የመጣውን ወራሪ ሃይል የመከቱበት እና ለነጻነታቸው ያደረጉትን ትግል ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ስፍራ ነው ያሉ ሲሆን ድሉ ለኢትዮጵያዊያን ብቻ ሳይሆን ለመላው አፍሪካዊያን ነጻነትን ያቀዳጀ ነው ብለዋል፡፡
በአፍሪካ የነጻነት ታሪክ ውስጥ ኢትዮጵያ ደማቅ አሻራ እንዳሳረፈች ተመልክቻለሁ ያሉት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሚካኤል ቹዳኮቭ፤ ኢትዮጵያዊያን ሲተባበሩ እና አንድ ሲሆኑ ድል ማግኘት እንዳለ እና ነጻነት እንደሚታወጅ ለሁሉም አፍሪካዊያን እና የአለም ህዝቦች ማሳያ ነው ማለታቸዉን የዓድዋ ድል መታሰቢያ ለኤኤምኤን የላከዉ መረጃ ያመላክታል፡፡